እንደዚሁ አምላክህ አንተን ይቅር አለህ፤ እኛም ወደዚህ ሀገር ከደረስን ጀምሮ እስከ ዛሬ ከኀዘን አላረፍንምና የሕዝቡን መከራ እንዳታይ ወደ ባቢሎን ትመጣ ዘንድ አልተወህም። ወደዚህ ሀገር ከመጣን ጀምሮ ለስድሳ ስድስት ዓመታት ከኀዘን አላረፍንም።