ሁለተኛም ከከተማ ርቆ ወጣ፤ እያዘነም ተቀመጠ፤ ሲሄድም አያውቅም ነበር፤ የበለሱንም ሙዳይ አኖረ፤ “ይህን ድንቁርና እግዚአብሔር ከእኔ እስኪያርቅልኝ ድረስ በዚህ እቀመጣለሁ” አለ።