ሁለቱም ሁሉ ተቀምጠው አለቀሱ፤ በማግሥቱም በነጋ ጊዜ ኤርምያስ አቤሜሌክን፥ “ሙዳዩን ይዘህ ወደ አግሪጳስ የወይን ቦታ በተራራው ጎዳና ሂድ፤ የእግዚአብሔር ረድኤት፥ ጌትነቱም በአንተ ራስ አድሯልና ለታመሙ ወገኖች ጥቂት በለስን አምጣ” ብሎ ላከው።