ኢዮብ በእግዚአብሔር አመነ፤ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ማመስገንን ቸል አላለምና የአዳም ልጆች ጠላት ዲያብሎስ ካመጣበት መከራውም ሁሉ አዳነው፤ በደረሰበትም መከራ ልቡን አላሳዘነም፤ ነገር ግን “እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔርም ነሳ፤ እግዚአብሔርም እንደ ወደደ ሆነ፤ በሁሉም በሰማይና በምድር የእግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን” አለ።