“ከሞትን በኋላ አንነሣም” አትበሉ፤ ይኽን የሚናገሩና የሚያስቡ ሰዎችን በትንሣኤ ጊዜ እንዳይድኑ ዲያብሎስ ተስፋ ያስቈርጣቸዋልና፥ ትንሣኤም በደረሰችባቸው ጊዜ ያውቃሉ፤ ኀጢአታቸውን ያስብባቸው ዘንድ ባለ ማወቅ ኀጢአት የሠሩ ሰዎች በትንሣኤ ጊዜ ፈጽመው ያዝናሉ፤ በዚያች ቀን እንደሚነሡ አላመኑበትምና።