ባልንጀራህን እንደ ራስህ እየወደድህ፥ ክፉ ባደረገብህ ሰውም ክፉ ነገር ሳታደርግ፥ መከራውን ለታገሡ ሰዎች ወደ ተሰጠ ማደሪያም ትገባ ዘንድ፥ ቅድስት ምድርን በትዕግሥትና በዕውቀት፥ በትንሣኤም ጊዜ መንግሥተ ሰማይን ተስፋ በማድረግ ከወረስዋት ሰዎች ጋር ዋጋህን ይሰጥህ ዘንድ ነው።