2 ሳሙኤል 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም ከሶርያ ከሞዓብና ከአሞን ልጆች፥ ከፍልስጥኤማውያንም፥ ከአማሌቅም፥ ከረአብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር ምርኮ ያመጣው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና ሞዓብ፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር የወሰደውን ምርኮ ለእግዚአብሔር ቀደሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና ሞዓብ፥ አሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከጾባ ንጉሥ ከረሖብ ልጅ ከሀዳድዔዜር የወሰደውን ምርኮ ለጌታ ቀደሰ። |
የአሞን ልጆችም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተማዪቱም ገቡ፤ ኢዮአብም ከአሞን ልጆች ዘንድ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
ዳዊትም ሞዓባውያንን መታ፤ በምድርም ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፤ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ለሕይወት ሰፈራቸው፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
ንጉሡም ዳዊት ከአሕዛብ ሁሉ ከኤዶምና ከሞዓብ፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከፍልስጥኤማውያንም፥ ከአማሌቅም ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
ዳዊትና ሰዎቹም ወጥተው በጌሴራውያንና በአማሌቃውያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እነዚህንም ቅጽር ባላቸው በጌላምሱርና በአኔቆንጦን እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ተቀምጠው አገኙአቸው።
ዳዊትም ሄዶ የአጥቢያ ኮከብ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግመኛም በማግሥቱ መታቸው፤ ከእነርሱም በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ጐልማሶች በቀር አንድም ያመለጠ የለም።