እግዚአብሔርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግዚአብሔርም በዚያው ቀሠፈው። በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት በዚያው ሞተ።
2 ሳሙኤል 6:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ገደለው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም “ዖዛ የሞተበት” ተባለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቍጣ ዖዛንን ስለ ሰበረው፣ ዳዊት ተከፋ፤ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፔሬዝ ዖዛ ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ቁጣ ዖዛን ስለሰበረው ዳዊት አዘነ፤ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፌሬጽ ዑዛ ተብሎ ይጠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የዚያ ስፍራ ስም “ፌሬጽዑዛ” እየተባለ ሲጠራ ይኖራል፤ እግዚአብሔር በቊጣ ተነሣሥቶ ዑዛን በመግደሉ ዳዊት እጅግ ተበሳጨ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ሰበረው ዳዊት አዘነ፥ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዖዛ ስብራት ተብሎ ተጠራ። |
እግዚአብሔርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግዚአብሔርም በዚያው ቀሠፈው። በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት በዚያው ሞተ።
እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “በውኑ ስለዚች ቅል ታዝናለህን?” አለው። እርሱም፥ “እስክሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ” አለ።