La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በረ​ኛ​ዪ​ቱም ስንዴ ታበ​ጥር ነበር፤ አን​ቀ​ላ​ፍ​ታም ተኝታ ነበር፤ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾቹ ሬካ​ብና በዓ​ናም በቀ​ስታ ወደ ቤት ገቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስንዴ እንደሚፈልግም ሰው ሆነው ወደ ቤቱ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ሆዱ ላይ ወጉት። ከዚያም ሬካብና ወንድሙ በዓና ሹልክ ብለው ወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆም ስንዴ እንደሚፈልግም ሰው ሆነው ወደ ቤቱ ውስጥ ዘልቀው በመግባት ሆዱ ላይ ወጉት። ከዚያም ሬካብና ወንድሙ በዓና አመለጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጠባቂዋ ሴት ስንዴ እያበጠረች በበር ላይ ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፤ ስለዚህም ሬካብና በዓና በቀስታ አልፈው ገቡ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በረኛይቱም ስንዴ ታበጥር ነበር፥ አንቀላፍታም ተኝታ ነበር፥ ሬካብና ወንድሙ በዓናም በቀስታ ገቡ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 4:6
5 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ከእ​ርሱ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። አበ​ኔ​ርም በጦሩ ጫፍ ወገ​ቡን ወጋው፤ ጦሩም በኋ​ላው ወጣ፤ በዚ​ያም ስፍራ ወድቆ በበ​ታቹ ሞተ። አሣ​ሄ​ልም ወድቆ በሞ​ተ​በት ስፍራ የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ይቆም ነበር።


አሜ​ሳይ ግን በኢ​ዮ​አብ እጅ ከነ​በ​ረው ሰይፍ አል​ተ​ጠ​ነ​ቀ​ቀም ነበር፤ ኢዮ​አ​ብም ሆዱን ወጋው፤ አን​ጀ​ቱ​ንም በም​ድር ላይ ዘረ​ገ​ፈው፤ ሁለ​ተ​ኛም አል​ወ​ጋ​ውም፤ ሞተም። ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም የቢ​ኮ​ሪን ልጅ ሳቡ​ሄን አሳ​ደዱ።


አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።


ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለኢ​ያ​ቡ​ስቴ የጭ​ፍራ አለ​ቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስም በዓና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብ​ን​ያ​ምም ልጆች የቤ​ሮ​ታ​ዊው የሬ​ሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮ​ትም ለብ​ን​ያም ተቈ​ጥራ ነበር።


እስ​ከ​ሚ​ታ​ወ​ኩም ድረስ ናዖድ አመ​ለጠ፤ ያወ​ቀ​ውም የለም፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አልፎ ወደ ሴይ​ሮታ አመ​ለጠ።