በጦር ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፥ ለይሁዳም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።
2 ሳሙኤል 3:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በመቃብሩ አጠገብ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ ለአበኔር አለቀሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አበኔርን በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም ጮኾ በአበኔር መቃብር ላይ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔር በኬብሮን ተቀበረ፤ በመቃብሩም ላይ ንጉሡ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እርሱን በማየት በመረረ ሁኔታ አለቀሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፥ ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በአበኔር መቃብር አጠገብ አለቀሰ፥ ሕዝቡም ሁሉ አለቀሱ። ንጉሡም ለአበኔር፦ |
በጦር ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፥ ለይሁዳም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።
ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፤ በበሩም ላይ ወዳለችው ሰገነት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ እኔ እንድሞት ቤዛህም እንድሆን ማን ባደረገኝ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።
ዳዊትም ጐልማሶቹን አዘዘ፤ ገደሉአቸውም፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። የኢያቡስቴን ራስ ግን ወስደው በአበኔር መቃብር በኬብሮን ቀበሩት።