ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤልያብ ልጅ የኬጤያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለው።
2 ሳሙኤል 23:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኬጤያዊው ኦርዮ፤ ሁሉም በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ። በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሒታዊው ኦርዮ፤ በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉ በሁሉ ሠላሳ ሰባት ናቸው። |
ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤልያብ ልጅ የኬጤያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለው።
አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኬጤያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፤ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።
ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።
ዳዊትም ኬጤያዊዉን አቤሜሌክንና የሶርህያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው፤ አቢሳም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እገባለሁ” አለ።