ከጻድቅ ጋር ጻድቅ ትሆናለህ፤ ከንጹሕ ሰውም ጋር ንጹሕ ትሆናለህ፤
“ለታማኝ ሰው ታማኝ መሆንህን፣ ለፍጹም ሰው ፍጹም መሆንህን ታሳያለህ።
“ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ ሆነህ ትገኛለህ፥ ለቅን ሰው አንተም ቅን ሆነህ ትታያለህ።
አምላክ ሆይ! ለአንተ ታማኞች ለሆኑት ታማኝ ነህ፤ እውነተኞች ለሆኑትም እውነተኛ ነህ።
ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፥ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፥
ከተመረጠም ጋር የተመረጠ ትሆናለህ፤ ከጠማማ ጋርም ጠማማ ትሆናለህ።
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፤ይማራሉና።
ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።