2 ሳሙኤል 18:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አይቶ፣ ዘበኛውን ተጣራና፣ “እነሆ ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለ። ንጉሡም፣ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውን ተጣራና፥ “ተመልከት! ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም፥ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ ይሆናል” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘበኛውም እንደገና አንድ ሌላ ሰው እየሮጠ ሲመጣ አይቶ፥ የቅጽር በር ጠባቂውን በመጣራት “ተመልከት! ሌላም አንድ ሰው እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም “ይህኛውም መልካም ወሬ ይዞ የሚመጣ ሊሆን ይችላል” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ፈጥኖ ቀረበ። ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፥ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፦ እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ አለ። ንጉሡም፦ እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል አለ። |
ዘበኛውም፥ “የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማሖስ ሩጫ ይመስላል” አለ፤ “ንጉሡም፦ እርሱ መልካም ሰው ነው፤ መልካምም ወሬ ያመጣል” አለ።
ገብተውም በከተማው በር ጮኹ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፥ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ያገኘነው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም።”