እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፤ እንዲሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በምድር ላይ እንዳይቀር ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፤”
2 ሳሙኤል 14:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሴቲቱን፥ “ወደ ቤትሽ በሰላም ሂጂ፤ እኔም ስለ አንቺ አዝዛለሁ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ሴቲቱን፣ “አንቺ ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ ስለ ጕዳይሽ አስፈላጊውን ትእዛዝ እሰጣለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ሴቲቱን፥ “ወደ ቤትሽ ሂጂ፤ እኔም ስለ አንቺ ጉዳይ ትእዛዝ እሰጣለሁ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “ወደ ቤትሽ ተመልሰሽ ሂጂ፤ እኔም ስለ አንቺ ጉዳይ አዛለሁ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሴቲቱን፦ ወደ ቤትሽ ሂጂ፥ እኔም ስለ አንቺ አዝዛለሁ አላት። |
እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፤ እንዲሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በምድር ላይ እንዳይቀር ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፤”
የቴቁሔዪቱም ሴት ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኀጢአቱ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን” አለችው።
ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ።