አቤሴሎምም ብላቴኖቹን፥ “በእርሻዬ አጠገብ ያለችውን የኢዮአብን እርሻ እዩ፤ በዚያም ገብስ አለው፤ ሄዳችሁ በእሳት አቃጥሉት” አላቸው። የአቤሴሎምም ብላቴኖች እርሻውን አቃጠሉት። የኢዮአብም አሽከሮች ልብሶቻቸውን ቀድደው ተመልሰው፥ “የአቤሴሎም አሽከሮች እርሻህን በእሳት አቃጠሉት” ብለው ነገሩት።
2 ሳሙኤል 14:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ተነሥቶ ወደ አቤሴሎም ወደ ቤቱ መጣና፥ “ብላቴኖችህ እርሻዬን ስለምን አቃጠሉት?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ወደ አቤሴሎም ቤት ሄደ፣ “አገልጋዮችህ ለምንድን ነው ዕርሻዬን ያቃጠሉት?” ብሎ ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ ተነሥቶ ወደ አቤሴሎም ቤት መጣና፦ “አገልጋዮችህ ለምንድን ነው እርሻዬን ያቃጠሉት?” ብሎ ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብም ወደ አቤሴሎም ቤት ገሥግሦ ሄደና “አገልጋዮችህ የእርሻዬን ሰብል ያቃጠሉት ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ተነሥቶ ወደ አቤሴሎም ወደ ቤቱ መጣና፦ ባሪያዎችህ እርሻዬን ስለምን አቃጠሉት? አለው። |
አቤሴሎምም ብላቴኖቹን፥ “በእርሻዬ አጠገብ ያለችውን የኢዮአብን እርሻ እዩ፤ በዚያም ገብስ አለው፤ ሄዳችሁ በእሳት አቃጥሉት” አላቸው። የአቤሴሎምም ብላቴኖች እርሻውን አቃጠሉት። የኢዮአብም አሽከሮች ልብሶቻቸውን ቀድደው ተመልሰው፥ “የአቤሴሎም አሽከሮች እርሻህን በእሳት አቃጠሉት” ብለው ነገሩት።
አቤሴሎምም ኢዮአብን፥ “ከጌድሶር ለምን መጣሁ? በዚያም ተቀምጬ ቢሆን ይሻለኝ ነበር ብለህ እንድትነግረው ወደ ንጉሥ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና ብዬ ወደ አንተ ላክሁ፤ አሁንም የንጉሡን ፊት አላየሁም፤ ኀጢአት ቢኖርብኝ ይግደለኝ” አለው።