ኢዮአብም በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሡንም አመሰገነ፤ ኢዮአብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ነገር አድርገሃልና በዐይንህ ፊት ሞገስን እንዳገኘ አገልጋይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።
2 ሳሙኤል 14:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ተነሥቶ ወደ ጌድሶር ሄደ፤ አቤሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ወደ ጌሹር ሄዶ አቤሴሎምን ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ ወደ ገሹር ሄዶ አቤሴሎምን ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተነሥቶም ወደ ገሹር ሄደ፤ አቤሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ አመጣው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ተነሥቶ ወደ ጌሹር ሄደ፥ አቤሴሎምንም ወደ ኢየሩሳሌም ይዞ መጣ። |
ኢዮአብም በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሡንም አመሰገነ፤ ኢዮአብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ነገር አድርገሃልና በዐይንህ ፊት ሞገስን እንዳገኘ አገልጋይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።
ሁለተኛውም ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቤግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌድሶር ንጉሥ ከቶልሜልም ልጅ ከመዓክ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ።
የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌርጋሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከዚች ቀን ድረስ በስሙ አውታይ ኢያዕር ብሎ ጠራ።