ያችም ሴት፥ “ለመግደል ባለ ደሞች እንዳይበዙ፤ ልጄንም እንዳይገድሉብኝ ንጉሥ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ያስብ” አለች። እርሱም፥ “የልጅሽስ አንዲት የራሱ ጠጕር በምድር ላይ እንዳትወድቅ ሕያው እግዚአብሔርን” አላት።
2 ሳሙኤል 14:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኢዮአብን፥ “እነሆ፥ ይህን ነገር አድርጌአለሁ፤ ሂድና ብላቴናውን አቤሴሎምን መልሰው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ኢዮአብን፣ “መልካም ነው፤ ፈቅጃለሁ፤ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን መልሰህ አምጣው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኢዮአብን፥ “እነሆ፥ ፈቅጃለሁ፤ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን መልሰህ አምጣው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ዘግየት ብሎ ኢዮአብን “ተስማምቼአለሁና ሄደህ ያንን ወጣት አቤሴሎምን ፈልገህ ወደዚህ አምጣው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ኢዮአብን፦ እነሆ፥ ይህን ነገር አድርጌአለሁ፥ እንግዲህ ሂድና ብላቴናውን አቤሴሎምን መልሰው አለው። |
ያችም ሴት፥ “ለመግደል ባለ ደሞች እንዳይበዙ፤ ልጄንም እንዳይገድሉብኝ ንጉሥ ፈጣሪው እግዚአብሔርን ያስብ” አለች። እርሱም፥ “የልጅሽስ አንዲት የራሱ ጠጕር በምድር ላይ እንዳትወድቅ ሕያው እግዚአብሔርን” አላት።
ኢዮአብም በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሡንም አመሰገነ፤ ኢዮአብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ነገር አድርገሃልና በዐይንህ ፊት ሞገስን እንዳገኘ አገልጋይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።
እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኀጢኣቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል” አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም።