አሁንም ሕዝቡ ስለሚያዩኝ ይህን ነገር ለጌታዬ ለንጉሥ እነግረው ዘንድ መጥቻለሁ፤ እኔም አገልጋይህ፦ የእኔን የአገልጋዩን ልመና ንጉሡ ያደርግልኝ እንደ ሆነ ለጌታዬ ለንጉሥ ልናገር፤
2 ሳሙኤል 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔንና ልጄን ከእግዚአብሔር ርስት ያርቀን ዘንድ ከሚሻ ሰው እጅ ያድን ዘንድ ንጉሡ አገልጋዩን ይሰማል አልሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከሰጠን ርስት እኔንም ልጄንም ሊነቅለን ከተነሣው ሰው እጅ ንጉሡ አገልጋዩን ሊታደግ ይፈቅድ ይሆናል።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘እግዚአብሔር ከሰጠን ርስት እኔንም ልጄንም ሊያጠፋን ከተነሣው ሰው እጅ ንጉሡ አገልጋዩን ሊታደግ ይፈቅድ ይሆናል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምነግርህን አድምጠህ ልጄንና እኔን በማጥፋት እግዚአብሔር የራሱ ካደረገው ምድር ሊያስወግደን ከሚፈልገው ሰው ታድነኛለህ ብዬ አስቤ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋንና ልጅዋን ከእግዚአብሔር ርስት ያጠፋቸው ዘንድ ከሚሻ ሰው እጅ ያድን ዘንድ ንጉሡ ባሪያውን ይሰማል አልሁ። |
አሁንም ሕዝቡ ስለሚያዩኝ ይህን ነገር ለጌታዬ ለንጉሥ እነግረው ዘንድ መጥቻለሁ፤ እኔም አገልጋይህ፦ የእኔን የአገልጋዩን ልመና ንጉሡ ያደርግልኝ እንደ ሆነ ለጌታዬ ለንጉሥ ልናገር፤
በእስራኤል ኀያላን ዘንድ ሰላምን ከሚወድዱት አንድዋ ነኝ፤ አንተ ግን በእስራኤል ያለችውን ከተማና እናት ከተማን ለማፍረስ ትሻለህ፤ ስለምንስ የእግዚአብሔርን ርስት ታጠፋለህ?”
አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደሆነ፥ ቍርባንህን ይቀበል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ።