አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
2 ሳሙኤል 13:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ኰብልሎ ወደ ጌድሶር ሄደ፤ በዚያም ሦስት ዓመት ያህል ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎም ሸሽቶ ወደ ጌሹር ከሄደ በኋላ፣ በዚያ ሦስት ዓመት ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎም ሸሽቶ ወደ ገሹር ከሄደ በኋላ፥ በዚያ ሦስት ዓመት ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎም ኮብልሎ ወደ ጌሹር ሄደ፥ በዚያም ሦስት ዓመት ያህል ተቀመጠ። |
አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
ሴቲቱም አለች፥ “በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ስለምን አሰብህ? ወይስ ንጉሥ ያሳደደውን ስላላስመለሰ እንደ በደል ከንጉሥ አፍ ይህ ቃል ወጥቶአልን?
አቤሴሎምም ኢዮአብን፥ “ከጌድሶር ለምን መጣሁ? በዚያም ተቀምጬ ቢሆን ይሻለኝ ነበር ብለህ እንድትነግረው ወደ ንጉሥ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና ብዬ ወደ አንተ ላክሁ፤ አሁንም የንጉሡን ፊት አላየሁም፤ ኀጢአት ቢኖርብኝ ይግደለኝ” አለው።
እኔ አገልጋይህ በሶርያ ጌድሶር ሳለሁ፦ እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም ቢመልሰኝ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀርባለሁ ብዬ ስእለት ተስዬ ነበርና” አለው።
ሁለተኛውም ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቤግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌድሶር ንጉሥ ከቶልሜልም ልጅ ከመዓክ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ።