ብላቴኖቹም፥ “ይህ ስለ ሕፃኑ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? እርሱ በሕይወት ሳለ ጾምህና አለቀስህ፤ እንቅልፍም አጣህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ፤ ጠጣህም” አሉት።
2 ሳሙኤል 13:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተናግሮም በጨረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲያው የንጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ደግሞም ንጉሡና ብላቴኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የንጉሡ ልጆች ጮኸው እየተላቀሱ ገቡ፤ እንደዚሁም ንጉሡና አገልጋዮቹ ሁሉ እጅግ አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ተናግሮ እንዳበቃ፥ የንጉሡ ልጆች ጮኸው እየተላቀሱ ገቡ፤ እንደዚሁም ንጉሡና አገልጋዮቹ ሁሉ አምርረው አለቀሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የዳዊት ልጆች ገብተው መላቀስ ጀመሩ፤ ዳዊትና መኳንንቱም በመረረ ሁኔታ አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተናግሮም በጨረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ ወዲያው የንጉሥ ልጆች ገቡ፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፥ ደግሞ ንጉሡና ባሪያዎቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ። |
ብላቴኖቹም፥ “ይህ ስለ ሕፃኑ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? እርሱ በሕይወት ሳለ ጾምህና አለቀስህ፤ እንቅልፍም አጣህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ፤ ጠጣህም” አሉት።
ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞ ከአፈቀራት ፍቅር ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፥ “ተነሥተሽ ሂጂ” አላት።
አቤሴሎም ግን ኰብልሎ ወደ መአክ ሀገር ወደ ጌድሶር ንጉሥ ወደ አሚሁድ ልጅ ወደ ቶልማይዮ ሄደ። ዳዊትም ሁል ጊዜ ለልጁ ያለቅስ ነበር።
ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፤ በበሩም ላይ ወዳለችው ሰገነት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ እኔ እንድሞት ቤዛህም እንድሆን ማን ባደረገኝ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።