2 ሳሙኤል 13:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፤ በምድር ላይም ወደቀ፤ በዙሪያውም ቁመው የነበሩ ብላቴኖቹ ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ተነሥቶ ቆመ፤ ልብሱን ቀደደ፤ በመሬትም ላይ ተዘረረ፤ በአጠገቡ ቆመው የነበሩት አገልጋዮቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፤ በመሬትም ላይ ተዘረረ፤ በአጠገቡ ቆመው የነበሩት አገልጋዮቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ከተቀመጠበት በመነሣት በሐዘን ልብሱን ቀዶ በመሬት ላይ ተዘረረ፤ በዚያ ከእርሱ ጋር የነበሩ አገልጋዮቹም በሐዘን ልብሳቸውን ቀደው በአጠገቡ በአክብሮት ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፥ በምድር ላይም ወደቀ፥ ባሪያዎቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀድደው በአጠገቡ ቆሙ። |
ገናም በመንገድ ሲሄዱ ለዳዊት፥ “አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ገደላቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልቀረም” የሚል ወሬ መጣ።
ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአበኔርም ፊት አልቅሱ” አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፤ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።