ትዕማርም፥ “ቀድሞ ከሠራኸው ክፋት ይልቅ እኔን በማውጣትህ የበለጠ ክፋት ትሠራለህ” አለችው፤ አምኖን ግን ቃልዋን አልሰማትም።
2 ሳሙኤል 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበር ቁሞ የሚያገለግለውንም ብላቴና ጠርቶ፥ “ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን ዝጋባት” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግል የሚያገለግለውን ወጣት ጠርቶ፣ “ይህችን ሴት ከዚህ አስወጣና በሩን ዝጋባት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጣት አገልጋዩንም ጠርቶ፥ “ይህቺን ሴት ከፊቴ አስወጣና በሩን ዝጋባት” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግል አገልጋዩንም ጠርቶ “ይህችን ሴት ከፊቴ ወዲያ አስወግድልኝ! እርስዋንም ወደ ውጪ አስወጥተህ በሩን ዝጋ!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያገለግለውንም ብላቴና ጠርቶ፦ ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን ዝጋባት አለው። |
ትዕማርም፥ “ቀድሞ ከሠራኸው ክፋት ይልቅ እኔን በማውጣትህ የበለጠ ክፋት ትሠራለህ” አለችው፤ አምኖን ግን ቃልዋን አልሰማትም።
ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፤ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ እንዲህ ያለውን ልብስ ይለብሱ ነበርና፤ አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን ዘጋባት።