2 ሳሙኤል 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምኖንም ትዕማርን፥ “በእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው” አላት፤ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አምኖን ትዕማርን፣ “እንድታጐርሺኝ ምግቡን እዚሁ መኝታ ክፍሌ አምጪልኝ” አላት። ትዕማርም ያዘጋጀችውን እንጀራ ይዛ ወንድሟ አምኖን ወዳለበት መኝታ ክፍል ገባች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አምኖን ትዕማርን፥ “እንድታጐርሺኝ ምግቡን እዚሁ መኝታ ክፍሌ አምጪልኝ” አላት። ትዕማርም ያዘጋጀችውን እንጀራ ይዛ ወንድሟ አምኖን ወዳለበት መኝታ ክፍል ገባች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ አምኖን ትዕማርን “ታጐርሺኝ ዘንድ ምግቡን ይዘሽ ወደ አልጋዬ አምጪው” አላት፤ ስለዚህም ትዕማር ምግቡን ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን አመጣችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምኖንም ትዕማርን፦ ከእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው አላት፥ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው። |
ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።