ፍላጻም የሚወረውሩ በቅጥሩ ላይ ሆነው በአገልጋዮችህ ላይ ወረወሩ፤ ከንጉሡም ብላቴኖች አንዳንድ ሞቱ፤ አገልጋይህ ኬጤያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ” አለው።
2 ሳሙኤል 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም መልእክተኛውን፥ “ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፥ አንድ ጊዜም ያን ይበላልና ይህ ነገር በዐይንህ አይክፋ፤ ከተማዪቱን የሚወጉትን አበርታ፤ አፍርሳትም ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፤ አንተም አጽናው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም፣ መልእክተኛውን፣ “እንግዲህ እንዲህ ብለህ ይህን ለኢዮአብ ንገረው፤ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ትበላለችና በዚህ አትዘን፤ በከተማዪቱ ላይ ጦርህን አጠንክር’ ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፥ መልእክተኛውን፥ “እንግዲህ እንዲህ ብለህ ይህን ለኢዮአብ ንገረው፤ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፥ ሌላ ጊዜም ሌላውን ትበላለችና በዚህ አትዘን’ ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም መልእክተኛውን “እንዲህ ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፦ በጦርነት ላይ ማን እንደሚሞት በቅድሚያ ስለማይታወቅ ‘አይዞህ በርታ’ በለው፤ ብስጭት እንዳያድርበትም ንገረው፤ ይልቁንም ኀይሉን አጠናክሮ አደጋ በመጣል ከተማይቱን እንዲይዝ አስጠንቅቀው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም መልእክተኛውን፦ ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜም ያን ያጠፋልና ይህ ነገር በዓይንህ አይክፋ፥ ከተማይቱን የሚወጉትን አበርታ፥ አፍርሳትም ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፥ አንተም አጽናው አለው። |
ፍላጻም የሚወረውሩ በቅጥሩ ላይ ሆነው በአገልጋዮችህ ላይ ወረወሩ፤ ከንጉሡም ብላቴኖች አንዳንድ ሞቱ፤ አገልጋይህ ኬጤያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ” አለው።
ወደምትሄድበትም ተመልከቱ፤ በድንበሩም መንገድ ላይ ወደ ቤትሳሚስ ብትወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እርሱ ነው፤ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን።”