መልእክተኛውም ዳዊትን፥ “ሰዎቹ በረቱብን፤ ወደ ሜዳም ወጡብን፤ እኛም እስከ በሩ መግቢያ ድረስ አሳደድናቸው።
መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ ዐየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳድደን መለስናቸው።
መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ አየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳደን መለስናቸው።
“ጠላቶቻችን ስለ በረቱብን እኛን ለመውጋት ከከተማይቱ ወጥተው ወደ ሜዳ መጡ፤ እኛ ግን አሳደን ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር መለስናቸው።
መልእክተኛውም ዳዊትን፦ ሰዎቹ በረቱብን፥ ወደ ሜዳም ወጡብን፥ እኛም ወደቅንባቸው፥ እስከ ከተማይቱም በር ድረስ ተከተልናቸው።
የኢዮአብም መልእክተኛ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንጉሡ ሄደ። ደርሶም ኢዮአብ የነገረውን የጦርነቱን ዜና ሁሉ ለዳዊት ነገረው። ዳዊትም በኢዮአብ ላይ ተቈጣ። ያንም መልእክተኛ፥ “ትዋጉ ዘንድ ወደ ከተማዋ ቅጥር ለምን ቀረባችሁ? በቅጥሩም እንደምትቈስሉ አታውቁምን? የይሩበዓል ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? አንዲት ሴት ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላበት በቴቤስ የሞተ አይደለምን? ስለምን ወደ ቅጥሩ ቀረባችሁ?” አለው።
ፍላጻም የሚወረውሩ በቅጥሩ ላይ ሆነው በአገልጋዮችህ ላይ ወረወሩ፤ ከንጉሡም ብላቴኖች አንዳንድ ሞቱ፤ አገልጋይህ ኬጤያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ” አለው።