የአሞን ልጆችም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተማዪቱም ገቡ፤ ኢዮአብም ከአሞን ልጆች ዘንድ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
2 ሳሙኤል 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ በአንድነት ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሶርያውያን በእስራኤላውያን እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ፣ እንደ ገና ተሰባሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሶርያውያን በእስራኤላውያን እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ፥ እንደገና ተሰባሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶርያውያን በእስራኤላውያን ድል እንደ ተመቱ በተገነዘቡ ጊዜ ሠራዊታቸውን ሁሉ በአንድነት አሰባሰቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ በአንድነት ተሰበሰቡ። |
የአሞን ልጆችም ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተማዪቱም ገቡ፤ ኢዮአብም ከአሞን ልጆች ዘንድ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።
አድርአዛርም ልኮ በካላማቅ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን ሰበሰባቸው፤ ወደ ኤላምም መጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶቤቅ በፊታቸው ነበረ።
የእሳት ኀይልን አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ።