ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ።
2 ሳሙኤል 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ከሶርያውያን ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እነርሱም ከፊቱ ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብና ዐብሮት የነበረው ሰራዊት ሶርያውያንን ለመውጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ ሶርያውያንም ከፊቱ ሸሹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ሶርያውያንን ለመውጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ ሶርያውያንም ከፊቱ ሸሹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብና ሠራዊቱ አደጋ ለመጣል ወደ ፊት በገሠገሡ ጊዜ ሶርያውያን ሸሹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ከሶርያውያን ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፥ እነርሱም ከፊቱ ሸሹ። |
ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ።