በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰፈር ከሳኦል ወገን አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት።
2 ሳሙኤል 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “ከወዴት መጣህ?” አለው፤ እርሱም፥ “ከእስራኤል ሰፈር አምልጬ መጣሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም፣ “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “ከእስራኤላውያን ሰፈር ሸሽቼ መምጣቴ ነው” በማለት መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም፥ “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ መጣሁ” በማለት መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ ከወዴት መጣህ? አለው፥ እርሱም፦ ከእስራኤል ሰፈር ኮብልዬ መጣሁ አለው። |
በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰፈር ከሳኦል ወገን አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት።
ዳዊትም፥ “ነገሩ ምንድን ነው? እስኪ ንገረኝ” አለው። እርሱም መልሶ፥ “ሕዝቡ ከሰልፉ ሸሽቶአል፤ ከሕዝቡም ብዙው ወደቁ፤ ሞቱም፤ ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ደግሞ ሞተዋል” አለው።
ከዚህም በኋላ ገብቶ፥ በጌታው ፊት ቆመ፤ ኤልሳዕም፥ “ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም፥ “እኔ አገልጋይህ ወዴትም አልሄድሁም” አለ።
ዳዊትም፥ “አንተ የማን ነህ? ከወዴት መጣህ?” አለው። ያም ግብፃዊ ብላቴና፥ “እኔ የአማሌቃዊ ባሪያ ነኝ፤ ከሦስት ቀንም በፊት ታምሜ ነበርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።