እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
2 ጴጥሮስ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውንም ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋራ አድኖ፣ ለቀድሞው ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ፥ ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ፥ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች በነበሩበት ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ሲያመጣ ራርቶ የቀድሞውን ዓለም አልማረውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ፥ |
እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
ወደ ጥልቁ ከሚወርዱት ጋር ወደ ቀደሙት ሕዝብ አወርድሻለሁ። በምድርም ላይ በሕይወትሽ ጸንተሽ እንዳትኖሪም ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ቀድሞ በፈረሰው ቤት ከምድር በታች አኖርሻለሁ።
ኖኅም ስለማይታየው ነገር የነገሩትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መርከብን ሠራ፤ በዚህም ዓለምን አስፈረደበት፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።