የእግዚአብሔርንም ከተማ ያጠፉ ዘንድ በመስጴጦምያ-ጌላቡሄ ሸለቆዎች እስከ ሶርያ ድረስ ሰፈሩ፤ በዚያም ኢሎፍላውያንንና አማሌቃውያንን ለመነ፤ በወንጀልም ከእርሱ ጋራ አንድ ይሆኑ ዘንድ ብዙ ወርቅንና ብርን፥ ፈረሶችንና ሠረገላዎችን ሰጣቸው።