ውኃው ወዳለበትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ የሚሞት፥ የሚመክንም አይኖርም” አለ።
2 ነገሥት 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ሰው፥ “የወደቀው ወዴት ነው?” አለ፤ ስፍራውንም አሳየው፤ ከእንጨትም ቅርፊት ቀርፎ በዚያ ጣለው፤ ብረቱም ተንሳፈፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም ሰው፣ “በየት በኩል ነው የወደቀው?” ሲል ጠየቀ። ቦታውን ባሳየውም ጊዜ ኤልሳዕ ዕንጨት ቈርጦ ወደ ውሃው ውስጥ በመጣል መጥረቢያውን እንዲንሳፈፍ አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “በየት በኩል ነው የወደቀው?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም መጥረቢያው የወደቀበትን ስፍራ ባሳየው ጊዜ እርሱ አንድ እንጨት ቆርጦ ወደ ውሃው ውስጥ በመጣል መጥረቢያው እንዲንሳፈፍ አደረገው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “በየት በኩል ነው የወደቀው?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም መጥረቢያው የወደቀበትን ስፍራ ባሳየው ጊዜ እርሱ አንድ እንጨት ቈርጦ ወደ ውሃው ውስጥ በመጣል መጥረቢያው እንዲንሳፈፍ አደረገው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ሰው “የወደቀው ወዴት ነው?” አለ ስፍራውንም አሳየው፤ እንጨትም ቆርጦ በዚያ ጣለው፤ ብረቱም ተንሳፈፈ። |
ውኃው ወዳለበትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ የሚሞት፥ የሚመክንም አይኖርም” አለ።
ኤልሳዕም፥ “ዶቄት አምጣና በምንቸቱ ውስጥ ጨምረው” አለው፥ ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ለሕዝቡ መልስላቸው ይብሉ” አለው። ከዚህም በኋላ በምንቸቱ ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም።
ከእነርሱም አንዱ ዛፉን ሲቈርጥ የምሳሩ ብረት ወልቆ ወደ ውኃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወየው! ወየው! የተዋስሁት ነበር” ብሎ ጮኸ።
ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ዕንጨትን አሳየው፤ በውኃውም ላይ ጣለው፤ ውኃውም ጣፈጠ። በዚያም ሥርዐትንና ፍርድን አደረገላቸው፤ በዚያም ፈተናቸው።