እርሱም አቀረበላቸው፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል በሉ፤ አተረፉም።
ከዚያም አቀረበላቸው፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም በልተው ተረፋቸው።
ስለዚህም አገልጋዩ ምግቡን አቀረበላቸው፤ እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላም የተረፈ ምግብ ነበር።
እንዲሁም በፊታቸው አኖረው፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል በሉ፤ አተረፉም።
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።
ሁሉም በሉና ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሡ።
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ያነሡትም የተረፈው ቍርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።
እነርሱም ሰበሰቡ፥ በልተው ከጠገቡ በኋላም ከአምስቱ የገብስ እንጀራ የተረፈው ቍርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።