ራሔልም ለያዕቆብ ልጅ እንዳልወለደች በአየች ጊዜ በእኅቷ ላይ ቀናችባት፤ ያዕቆብንም “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ከአልሆነ እሞታለሁ” አለችው።
2 ነገሥት 4:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፥ “በውኑ ከጌታዬ ልጅን ለመንሁን? እኔም አታታልለኝ አላልሁህምን?” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “ጌታዬ፤ ለመሆኑ እኔ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘አጕል ተስፋ እንዳትሰጠኝ’ አላልሁህምን?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም “ጌታዬ፥ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘የማይፈጸምስ የተስፋ ቃል አትስጠኝ’ ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቲቱም “ጌታዬ፥ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘የማይፈጸምስ የተስፋ ቃል አትስጠኝ’ ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም “በውኑ ከጌታዬ ልጅን ለመንሁን? እኔም ‘አታታልለኝ’ አላልሁህምን?” አለች። |
ራሔልም ለያዕቆብ ልጅ እንዳልወለደች በአየች ጊዜ በእኅቷ ላይ ቀናችባት፤ ያዕቆብንም “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ከአልሆነ እሞታለሁ” አለችው።
ኤልሳዕም፥ “በሚመጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት፤ እርስዋም፥ “አይደለም ጌታዬ ሆይ፥ አገልጋይህን አትዋሻት” አለችው።
ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኑር” አለው።