ጸሓፊውም ሳፋን ወደ ንጉሡ መጣ፤ ለንጉሡም፥ “በመቅደሱ የተገኘውን ገንዘብ አገልጋዮችህ አፈሰሱት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ሥራ ለመሥራት ለተመደቡት ሰዎች ሰጡት” ብሎ ነገረው።
2 ነገሥት 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቁ ካህንም ኬልቅያስ ጸሓፊውን ሳፋንን፥ “የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤት አግኝቻለሁ” አለው፤ ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው፥ እርሱም አነበበው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ ጸሓፊውን ሳፋንን፣ “የሕጉን መጽሐፍ እኮ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አገኘሁት” ብሎ ሰጠው፤ እርሱም ተቀብሎ አነበበው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ጸሐፊው ሳፋን ከንጉሡ የተላከውን ትእዛዝ ለሒልቂያ ሰጠ፤ ሒልቂያም “የሕጉን መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘሁ” ብሎ ለሳፋን ሰጠው፤ ሳፋንም ተቀብሎ አነበበው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጸሐፊው ሳፋን ከንጉሡ የተላከውን ትእዛዝ ለሒልቂያ ሰጠ፤ ሒልቂያም “የሕጉን መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘሁ” ብሎ ለሳፋን ሰጠው፤ ሳፋንም ተቀብሎ አነበበው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ኬልቅያስ ጸሐፊውን ሳፋንን “የሕጉን መጽሐፍ በእግዚአብሔር ቤት አግኝቻለሁ፤” አለው፤ ኬልቅያስም መጽሐፉን ለሳፋን ሰጠው፤ እርሱም አነበበው። |
ጸሓፊውም ሳፋን ወደ ንጉሡ መጣ፤ ለንጉሡም፥ “በመቅደሱ የተገኘውን ገንዘብ አገልጋዮችህ አፈሰሱት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ሥራ ለመሥራት ለተመደቡት ሰዎች ሰጡት” ብሎ ነገረው።
ንጉሡም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጣ፤ ከእርሱም ጋር የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ፥ ካህናቱና ነቢያቱም፥ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሾቹ ጀምሮ እስከ ታላቆቹ ድረስ ወጡ፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ በጆሮአቸው አነበበ።
ደግሞም ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈውን የሕጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መናፍስት ጠሪዎቹንና ጠንቋዮቹን ተራፊምንና ጣዖታትንም በይሁዳ ሀገርና በኢየሩሳሌም የተገኘውን ርኵሰት ሁሉ ኢዮስያስ አስወገደ።