የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ አናጢዎችንም፥ ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፤ ለዳዊትም ቤት ሠሩለት።
2 ነገሥት 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአናጢዎችና ለጠራቢዎች፥ ለድንጋይም ወቃሪዎች፥ መቅደሱንም ለመጠገን እንጨትንና የተወቀረውን ድንጋይ ለሚገዙ ይክፈሉት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚከፍሉትም ለየእጅ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ነው። እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ ዕድሳት ሥራ የሚሆኑ ዕንጨቶችና ጥርብ ድንጋዮች ይግዙበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚከፍሉትም ለአና ጺዎች፥ ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ነው። እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሥራ የሚሆኑ ሳንቃዎችና የተጠረቡ ድንጋዮች ይግዙበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአናጢዎችና ለጠራቢዎች፥ ለድንጋይ ወቃሪዎችም፥ መቅደሱንም ለመጠገን እንጨትንና የተወቀረውን ድንጋይ ለሚገዙ ይክፈሉት። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ አናጢዎችንም፥ ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፤ ለዳዊትም ቤት ሠሩለት።
የተናደውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠገን መክፈል ለሚያሻው ሁሉ ድንጋይንና እንጨትን ይገዙ ዘንድ፥ ለግንበኞችና ለድንጋይ ወቃሪዎች ይሰጡት ነበር።
በእግዚአብሔርም ቤት ላሉት ሠራተኞች አለቆች ይስጡት፤ እነርሱም የተናደውን የእግዚአብሔርን ቤት ለሚጠግኑት ሠራተኞች፥
ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ይሰበስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች ይወቅሩ ዘንድ ጠራቢዎችን አኖረ።