በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ፤ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አጋርዳታለሁ።”
2 ነገሥት 20:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢሳይያስም አለው፥ “የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተህ በእባጭህ ላይ አድርግ ትፈወሳለህም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢሳይያስ፣ “ትኵስ የበለስ ጥፍጥፍ አዘጋጁ” አላቸው፤ እነርሱም አዘጋጅተው ዕባጩ ላይ አደረጉለት፤ ተፈወሰም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢሳይያስ የንጉሡን አገልጋዮች፥ “የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ አምጡልኝ” ብሎ አመጡለት፤ በቁስሉ ላይ ባደረጉለት ጊዜ የሕዝቅያስ ቁስል ተፈወሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢሳይያስ የንጉሡን አገልጋዮች፥ “የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ አምጡልኝ” ብሎ አመጡለት፤ በቊስሉ ላይ ባደረጉለት ጊዜ የሕዝቅያስ ቊስል ተፈወሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢሳይስም “የበለስ ጥፍጥፍ አምጡልኝ፤” አለ፤ አምጥተውም በእባጩ ላይ አደርጉለት፤ እርሱም ተፈወሰ። |
በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ፤ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አጋርዳታለሁ።”
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ፥ እኔስ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንድወጣ ምልክቱ ምንድን ነው?” አለው።
ኤልሳዕም፥ “ዶቄት አምጣና በምንቸቱ ውስጥ ጨምረው” አለው፥ ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ለሕዝቡ መልስላቸው ይብሉ” አለው። ከዚህም በኋላ በምንቸቱ ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም።