2 ነገሥት 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከንፈር ቃል ለሰልፍ ምክርና ኀይል እንደሚሆን ትናገራለህ፤ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር ስልትና ኀይል አለኝ ትላለህ፤ ነገር ግን ባዶ ቃል ብቻ ትናገራለህ። በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተደግፈህ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቃላት ጋጋታ የጦርነትን ስልትና ኃይል የሚተካ ይመስልሃልን? ማን ይረዳኛል ብለህ ነው በአሦር ላይ ለማመፅ ያሰብከው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃላት ጋጋታ የጦርነትን ስልትና ኀይል የሚተካ ይመስልሃልን? ማን ይረዳኛል ብለህ ነው በአሦር ላይ ለማመፅ ያሰብከው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከንፈር ቃል ለሰልፍ ምክርና ኀይል እንደሚሆን ትናገራለህ፤ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው? |