2 ቆሮንቶስ 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የመንፈስ ቅዱስም አንድነት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። የመቄዶንያ ክፍል በምትሆን በፊልጵስዩስ ተጽፎ በቲቶና በሉቃስ እጅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተላከው ሁለተኛዉ መልእክት ተፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ አሜን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምእመናን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። |