2 ቆሮንቶስ 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛስ በማይገባ ሌላ በደከመበት አንመካም፤ ነገር ግን ሃይማኖታችሁ እንድትሰፋ፥ የተሠራችላችሁ ሕግም በእናንተ እንድትጸና ተስፋ እናደርጋለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ሌሎች በደከሙበት ሥራ ከመጠን በላይ በመመካት ከተመደበልን ወሰን አናልፍም፤ ይልቁንም እምነታችሁ እያደገ በሄደ ቍጥር በእናንተ ዘንድ የተመደበልን አገልግሎት እየሰፋ እንደሚሄድ ተስፋ እናደርጋለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሎች ድካም ያለ ልክ አንመካም፤ ነገር ግን እምነታችሁ ሲያድግ፥ የምንሠራበት ወሰን እየሰፋ ይሄዳል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ከወሰነልን ክልል አልፈን በሌሎች ሥራ ያለ ልክ አንመካም፤ ይልቅስ እምነታችሁ እንዲያድግና የእኛም ሥራ እግዚአብሔር በወሰነልን ክልል በእናንተ መካከል ይበልጥ እንዲስፋፋ ተስፋ እናደርጋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌሎች ድካም ያለ ልክ አንመካም፥ ነገር ግን እምነታችሁ ሲያድግ ከእናንተ ወዲያ ባለው አገር እስክንሰብክ ሥራችንን እየጨመርን፥ በክፍላችን በእናንተ ዘንድ እንድንከብር ተስፋ እናደርጋለን፤ በሌላው ክፍል ስለ ተዘጋጀው ነገር አንመካም። |
ወንጌልን ለማስተማር ተጋሁ፤ ነገር ግን በሌላ መሠረት ላይ እንዳላንጽ የክርስቶስ ስም ወደ ተጠራበት አልሄድሁም።
እኛስ ወደ እናንተ እስክንደርስ ድረስ እግዚአብሔር በወሰነልን ሕግና ሥርዐት እንጂ፥ ከዐቅማችን አልፈን እጅግ አንመካም።
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤