እንዲህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆማለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመከራችንም ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።
2 ዜና መዋዕል 6:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል ሁሉ፥ ማናቸውም ሰው ሕማሙንና ኀዘኑን ዐውቆ ጸሎትና ልመና ቢያደርግ፥ እጆቹንም ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝብህ ማንኛውም ሰው ወይም መላው እስራኤል ጭንቀቱንና ሕመሙን ዐውቆ እጆቹን ወደዚህ ቤት በመዘርጋት ማንኛውንም ጸሎትና ልመና በሚያቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል ሁሉ፥ እያንዳንዱም ሰው ሕመሙንና ኀዘኑን አውቆ ጸሎትና ልመና ቢያደርግ እጆቹንም ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብን የሚሰብር መሪር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል ሁሉ፥ ማናቸውም ሰው ሕመሙንና ኀዘኑን አውቆ ጸሎትና ልመና ቢያደርግ፥ እጆቹንም ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ፥ |
እንዲህም አሉ፦ ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆማለን፤ ስምህ በዚህ ቤት ላይ ነውና፤ በመከራችንም ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ።
“በምድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ፥ ወይም አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ ጠላቶቻቸውም የሀገሩን ከተሞች ከብበው ቢያስጨንቁአቸው፥ ማናቸውም መቅሠፍትና ደዌ ቢሆን፥
አንተ በተዘጋጀው በማደሪያህ በሰማይ ስማው፤ ይቅርም በለው፤ ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለው፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና።
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።