በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በኤማት ምድር ባለችው በዴብላታ አሰረው፤ በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት።
2 ዜና መዋዕል 36:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ወደ ግብፅ ወሰደው፤ በሀገሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የግብጽ ንጉሥ በኢየሩሳሌም ካለው ዙፋኑ አወረደው፣ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽም ንጉሥ ከኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አወረደው፥ በምድሪቱም በሚኖሩት ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ ኢዮአሐዝን እስረኛ አድርጎ ወሰደው፤ የይሁዳንም ሕዝብ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚመዝን ብርና ሠላሳ አራት ኪሎ የሚመዝን ወርቅ እንዲገብርለት አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግብጽም ንጉሥ በኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አወጣው፤ መቶም መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ዕዳ ጣለበት። |
በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ ፈርዖን ኒካዑ በኤማት ምድር ባለችው በዴብላታ አሰረው፤ በምድሩም ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ፈሰሴ ጣለበት።
ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ሦስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። 2 ‘ሀ’ የእናቱም ስም ከሎቤና የኤርምያስ ልጅ አሚጣል ነበረች። 2 ‘ለ’ አባቶቹ እንደ ሠሩት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራን ሠራ። በኢየሩሳሌምም እንዳይነግሥ በኤማት ምድር በዴብላታ ፈርዖን ኒካዑ ማርኮ አሰረው።
የግብፅም ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ የይሁዳን ንጉሥ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ ፋንታ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠ፤ ፈርዖን ኒካዑም ወንድሙን ኢዮአክስን ይዞ ወደ ግብፅ ወሰደው። በዚያም ሞተ። 4 ‘ሀ’ ወርቅንና ብርን ለፈርዖን ሰጠ። በዚያን ጊዜም ምድር በፈርዖን ትእዛዝ ብር መገበሯን ጀመረች። 4 ‘ለ’ እያንዳንዱም እንደሚችለው ለፈርዖን ኒካዑ እንዲገብር ከሀገሪቱ ሕዝብ ወርቅንና ብርን ጠየቀ።