2 ዜና መዋዕል 20:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባቱም በአሳ መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ቅን የሆነውን ነገር ከማድረግ ፈቀቅ አላለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በአካሄዱ ሁሉ የአባቱን የአሳን መንገድ ተከተለ፤ ከዚያም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔርም ፊት መልካም የሆነውን አደረገ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአባቱም በአሳ መንገድ ሄደ፥ ከእርሱም ፈቀቅ አላለም፤ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ እንደ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አደረገ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአባቱም በአሳ መንገድ ሄደ፤ ከእርሱም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔር ፊት ቅን አደረገ። |
በኮረብታ ላይ የነበሩትን መስገጃዎች ግን ከእስራኤል አላራቀም። ገና በእስራኤል ዘንድ እስከ አሁን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ነበረ።
ኢዮሣፍጥም በይሁዳ ላይ ነገሠ፤ መንገሥ በጀመረ ጊዜም የሠላሳ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳሊ ልጅ አዙባ ነበረች።
ነገር ግን ኮረብታዎች ገና በዚያ ነበሩ፤ ሕዝቡም ገና ልባቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር አላቀኑም ነበር።