እነዚህ ሁሉ የይዴኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
2 ዜና መዋዕል 17:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብንያምም ጽኑዕ ኀያል የነበረው ኤሊያዳ፥ ከእርሱም ጋር ቀስት የሚገትሩ፥ ወንጭፍ የሚወነጭፉ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺሕ ሰዎች ጋራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብንያምም ጽኑዕ ኃያል የነበረው ኤሊዳሄ፥ ከእርሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የሚይዙ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብንያም ነገድ ለተመለመሉት ወታደሮች ዋና አዛዥ ኤሊያዳዕ ተብሎ የሚጠራ ጀግና ወታደር ነበር፤ በእርሱም ሥር ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሺህ ወታደሮች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብንያምም ጽኑዕ ኃያል የነበረው ኤሊዳሄ፥ ከእርሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የሚይዙ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ |
እነዚህ ሁሉ የይዴኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
እርሱም የይሁዳን ሰዎች፥ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ቅጥርም፥ ግንብም፥ መዝጊያም፥ መወርወሪያም እናድርግባቸው፤ ምድሪቱንም እንገዛታለን፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንደ ፈለግነው እርሱም ይፈልገናልና፤ እርሱም በዙሪያችን ዕረፍት ሰጥቶናል፤ ሁሉንም አከናወነልን” አለ።
ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት፥ ወንጭፍ የሚወነጭፉ፥ ቀስትም የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ።
ከእርሱም በኋላ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የዝክሪ ልጅ ማስያስ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ነበሩ።
የጋድ ልጆች በየትውልዳቸው- በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥