የቀረውም የአብያ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ እነሆ፥ የተጻፈ አይደለምን? በአብያና በኢዮርብአም መካከል ሰልፍ ነበረ።
2 ዜና መዋዕል 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብያም ጸና፤ ዐሥራ አራት ሚስቶችንም አገባ፤ ሃያ ሁለትም ወንዶች ልጆችንና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብያ ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ ዐሥራ አራት ሚስቶች አግብቶም ሃያ ሁለት ወንዶችና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብያም ጸና፥ ዐሥራ አራትም ሚስቶች አገባ፥ ሀያ ሁለትም ወንዶች ልጆችንና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆች ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቢያ ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ ዐሥራ አራት ሚስቶችን አግብቶ ኻያ ሁለት ወንዶች ልጆችንና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብያም ጸና፤ ዐሥራ አራትም ሚስቶች አገባ፤ ሀያ ሁለትም ወንዶች ልጆችንና ዐሥራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ። |
የቀረውም የአብያ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ እነሆ፥ የተጻፈ አይደለምን? በአብያና በኢዮርብአም መካከል ሰልፍ ነበረ።
ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስድሳ ቁባቶች ነበሩት፤ ሃያ ስምንት ወንዶችና ስድሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።
ወደ አባቱም ቤት ወደ ኤፍራታ ገባ፤ ሰባ የሆኑትን የይሩበኣልን ልጆች ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው፤ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ነበርና ተረፈ።