1 ጢሞቴዎስ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልቴት በመዝገብ ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፤ የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን ያስፈልጋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት ያነሰ መበለት በመዝገብ ላይ አትጻፍ፤ ደግሞም የአንድ ባል ሚስት የነበረች ልትሆን ይገባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መበለቲቱ ከስልሳ ዓመት በታች ያልሆነች፤ የአንድም ባል ሚስት የነበረች በመዝገብ ትጻፍ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከስድሳ ዓመት በታች የሆነችን ባልዋ የሞተባትን ሴት በመበለቶች መዝገብ አትጻፍ፤ ደግሞም አንድ ባል ብቻ ያገባች እንድትሆን ያስፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልቴት በመዝገብ ብትጻፍ ዕድሜዋ ከስድሳ ዓመት እንዳያንስ፥ የአንድም ባል ሚስት የነበረች እንድትሆን ያስፈልጋል፤ |
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤