1 ሳሙኤል 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም መልሶ ሳኦልን፥ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬም ከእኔ ጋር ወደ ባማ ኮረብታ በፊቴ ውጣና ምሳ ብላ፤ ነገም በጥዋት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህም ያለውን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋራ ስለምትበሉ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጧት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ስለምትበሉ፤ ከፊቴ ቀድማችሁ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ውጡ፤ ነገ ጠዋት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህ ያለውንም እነግርሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም ሳኦልን፦ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር ስለምትበሉ ከእኔ በፊት ወደ ማምለኪያው ቀድመህ ውጣ፤ ነገ ጧት በልብህ ያለውን ሁሉ ነግሬህ አሰናብትሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም መልሶ ሳኦልን፦ ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከእኔ ጋር ትበላላችሁና በፊቴ ወደ ኮረብታው መስገጃ ውጡ፥ ነገም አሰናብትሃለሁ፥ በልብህም ያለውን ሁሉ እነግርሃለሁ፥ |
በልባቸው የደበቁትም ይገለጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማያምነው ተመልሶ ይጸጸታል፤ በግንባሩም ወድቆ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል፥ በእውነት እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለም ይናገራል።
ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አታስጨንቀው። የእስራኤል መልካም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን?” አለው።