1 ሳሙኤል 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም በበሩ ወደ ሳሙኤል ቀርቦ፥ “የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፣ “የባለራእዩ ቤት የት እንደ ሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም በቅጥሩ በር ላይ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፥ “የባለ ራእዩ ቤት የት እንደሆነ ትነግረኛለህ?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም በቅጽሩ በር አጠገብ ወደነበረው ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ “የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም በበሩ ወደ ሳሙኤል ቀርቦ፦ የባለ ራእዩ ቤት ወዴት እንደ ሆነ፥ እባክህ፥ ንገረኝ አለው። |
ሳሙኤልም መልሶ ሳኦልን፥ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬም ከእኔ ጋር ወደ ባማ ኮረብታ በፊቴ ውጣና ምሳ ብላ፤ ነገም በጥዋት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህም ያለውን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ፤