ከቤተ ሰቡም አንዱ እርሱንና ብላቴናውን፥ “ወዴት ሄዳችሁ ኖሮአል?” አላቸው። እነርሱም፥ “አህዮችን ልንፈልግ ሄደን ነበር፤ ባጣናቸውም ጊዜ ወደ ሳሙኤል መጣን” አሉት።
1 ሳሙኤል 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ብላቴናውን፥ “የተናገርኸው ነገር መልካም ነው፤ ና፤ እንሂድ” አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “መልካም፤ ና እንሂድ” አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ “መልካም፤ ና እንሂድ” አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም አገልጋዩን “መልካም ነው እንሂድ!” አለው፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ሰው ወደ አለበት ከተማ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ብላቴናውን፦ የተናገረኸው ነገር መልካም ነው፥ ና፥ እንሂድ አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። |
ከቤተ ሰቡም አንዱ እርሱንና ብላቴናውን፥ “ወዴት ሄዳችሁ ኖሮአል?” አላቸው። እነርሱም፥ “አህዮችን ልንፈልግ ሄደን ነበር፤ ባጣናቸውም ጊዜ ወደ ሳሙኤል መጣን” አሉት።
ቀድሞ ነቢዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበርና አስቀድሞ በእስራኤል ዘንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እንሂድ ይል ነበር።”