La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 6:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የወ​ር​ቁም አይ​ጦች ቍጥር ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች እንደ ነበ​ሩት ከተ​ሞች ሁሉ ቍጥር እን​ዲሁ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም እስከ ታላቁ ድን​ጋይ የሚ​ደ​ርሱ ቅጥር ያላ​ቸው ከተ​ሞ​ችና የፌ​ር​ዜ​ዎን መን​ደ​ሮች ናቸው። በዚ​ህም ድን​ጋይ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ድን​ጋ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤ​ት​ሳ​ሚ​ሳ​ዊው በኦ​ሴዕ እርሻ አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፣ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሳሚሳዊው በኢያሱ ዕርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ድንጋይ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም ከተላኩት መካከል በተመሸጉ ከተሞችና ቅጽር ባልተሠራላቸው መንደሮች ሆነው አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሩት በእያንዳንዱ ከተማ ስም በአይጥ አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች ነበሩ። በቤትሼሜሽ በሚኖረው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያኖሩበትም ታላቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይታያል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንዲቱ ለአቃሮን የወርቁም አይጦች ቁጥር ለአምስቱ የፍልስጥኤማውያን አለቆች እንደ ነበሩት ከተሞች ሁሉ ቁጥር እንዲሁ ነበረ፥ እነርሱም እስከ ታላቁ ድንጋይ የሚደርሱ ከተሞችና መንደሮች ናቸው። በዚህም ድንጋይ ላይ የእግዚአብሔርን ታቦት አስቀመጡ፥ ድንጋዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤትሳሚሳዊው በኢያሱ እርሻ አለ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 6:18
4 Referencias Cruzadas  

እጅግ ብዙ ከሆ​ኑት ከፌ​ር​ዜ​ዎን ከተ​ሞች ሌላ፥ እነ​ዚህ ከተ​ሞች ሁሉ ቁመቱ ረዥም በሆነ ቅጥር በመ​ዝ​ጊ​ያና በመ​ወ​ር​ወ​ሪ​ያም የተ​መ​ሸጉ ነበሩ።


በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤


እነ​ር​ሱም፥ “ስለ መቅ​ሠ​ፍቱ የም​ን​ሰ​ጠው የበ​ደል መባእ ምን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ን​ተ​ንና አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕዝ​ባ​ች​ሁ​ንም ያገ​ኘች መቅ​ሠ​ፍት አን​ዲት ናትና እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ቍጥር አም​ስት የወ​ርቅ እባ​ጮች፥ አም​ስ​ትም የወ​ርቅ አይ​ጦች አቅ​ርቡ።