የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዳግመኛ ሽማግሌዎችና ባልቴቶች በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፣ ሰውም ሁሉ ከዕድሜው ብዛት የተነሣ ምርኩዝ በእጁ ይይዛል።
1 ሳሙኤል 2:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤትህም ለዘለዓለም ሽማግሌ አይገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማደሪያዬም መከራ ታያለህ፤ ምንም እንኳ ለእስራኤል በጎ ነገር ቢደረግም፣ በቤተ ሰብህ ውስጥ ሽማግሌ ፈጽሞ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ በእስራኤል በረከት ሁሉ በማደሪያዬ ጠላትህን ታያለህ፤ በቤትህም ለዘለዓለም ሽማግሌ አይገኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እኔ በምመለክበት ቦታ ብዙ ችግር ታያለህ፤ በእስራኤል ዘንድ በጎ ነገር የሚደረግ ቢሆንም ከአንተ ቤተሰብ መካከል ማንም ረጅም ዕድሜ የሚኖረው አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል በረከት ሁሉ፥ በማደሪያዬ ጠላትህን ታያለህ በቤትህም ለዘላለም ሽማግሌ አይገኝም። |
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዳግመኛ ሽማግሌዎችና ባልቴቶች በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፣ ሰውም ሁሉ ከዕድሜው ብዛት የተነሣ ምርኩዝ በእጁ ይይዛል።
በዐይኖቹ የሚፈጽም በነፍሱም የሚተጋ ሰውን ከመሠዊያዬ አላጠፋም። ከቤትህ የሚቀሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጐልማሶች ሰይፍ ይሞታሉ።
ሕዝቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪሩቤልም ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።